Leilt Zenebwork Primary and medium School
Announcement 19ኛውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት ተከበረ ።

19ኛውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት ተከበረ ።

15th October, 2026

የልዕልት ዘነበወርቅ መታሰቢያ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 19ኛውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት አከበረ ።
ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ዕለቱ ገና በጠዋቱ በወርቃማው ሰኞ በት/ቤቱ ፍ/ር/መ/ር በፍቃዱ አባይነህ በተላለፈ የዕውቀት ሽግግር የጀመረ ነበር ። የት/ቤቱ ር/መ/ሮች ፣መምህራኖች ፡ሠራተኞች እና ተማሪዎች 19ኛውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባት እና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በድምቀት አከበሩ።
በዕለቱ የተማሪ ስካውት አባላት የሰንደቅ ዓላማ ሥነ-ሥርዓት ያደመቁና ሰነደቅ አላማውን በብሄራዊ መዝሙር ኣመላዊ የት/ቤቱ ማህበረሰብ ጋር 4፡30 በመዘመር የተከናወነ ሲሆን የት/ቤቱ ዋና ር/መር አቶ ፍቃዱ ታሪኩ እና ዩኒት ሊደር የዕለቱን አስፈላጊነት፣ የሰንደቅ ዓላማችንን ሀገራዊ እሴት የሚገልጹ መልዕክቶችንም አስተላልፈዋል። በመሆኑም በመልዕክቱ ለሀገር አንድነት መቆም የሁሉም ዜጋ ማኅበራዊና ሀገራዊ ኃላፊነት መሆኑንና ሰንደቅ አላማም የዚህ ክብር መገለጫ መሆኑ ተመላክቷል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with