Leilt Zenebwork Primary and medium School
Announcement አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የትምህርት ሴክተሩን የተከለሰ የ5 አመት ስትራቴጂክ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የትምህርት ሴክተሩን የተከለሰ የ5 አመት ስትራቴጂክ

15th October, 2026

ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ አምስት አመታት የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲጎለብት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ።


(ጥቅምት 5/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የትምህርት ሴክተሩን የተከለሰ የ5 አመት ስትራቴጂክ እና የ2019 የትምህርት ዘመን እቅድን ጨምሮ የ1ኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ሪፖርትና የ90 ቀን እቅድ ግምገማ አካሂደዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ልማት ስራው ውጤታማ ሆኖ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል ቢሮ የአምስት አመት ስትራቴጂክ እና የ2019 የትምህርት ዘመን እቅድን አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ጠቁመው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 94/2019 መሰረት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተሰጡ 22 ስልጣንና ተግባራትን በማካተት የ 5 ዓመቱ እንዲሁም የ2019 የትምህርት ዘመን እቅድ መከለሱ ገልጸዋል፡፡


ሀላፊው አክለዉም በስትራቴጂው የተቀመጡ ግቦች ተሳክተው የትምህርት ጥራት በሚፈለገው ደረጃ እንዲረጋገጥ ቢሮው ባለድርሻ አካላትን አስተባብሮ የሚሰራ መሆኑን በመግለጽ የአጠቃላይ ካውንስል አባላትም ስትራቴጂክ እቅዱ ስኬታማ እንዲሆን ትኩረት አድርገው መንቀሳቀስ የሚገባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with